ክፍል 1.10: የመስተጋብር መሰረታዊ - Holt International...መስተጋብር...

4
ምእራፍ 1| ክፍል 1.10: የመስተጋብር መሰረታዊ ሐሳቦች 101 ክፍል 1.10: የመስተጋብር መሰረታዊ ሐሳቦች መስተጋብር ማለት ምን ማለት ነው ? መስተጋብር ማለት በሌላ አገላለፅ ግንኙነትማለት ነው፡፡ እነዚህን ቃላቶች በዚህ መመሪያ ላይ እያለዋወጥን እንጠቀምባቸዋለን፡፡ ልጆች ከተንከባካቢዎቻቸው ጋር በየዕለቱ የሚጋሯቸው ግዜዎች የምገባን ግዜ ጨምሮ መስተጋብር ይባላል፡፡ ልጆች ጤናማ እንዲሆኑ እና እንዲበለፅጉ አዎንታዊ የታሰበባቸው ግንኙነቶች አስፈላጊ ናቸው፡፡ ልጁ ከአሳዳጊዎቹ ጋር ወጥነት እና ትኩረት ያለው ግንኙነት ሲኖረው፣ እድገቱ ይበልጥ ጠንካራ ይሆናል፡፡ በእብዛኛው ከሌሎች ጋር የሚከሰቱ አስደሳች ግንኙቶች የልጁን እድገት ያጠናክራሉ፡፡ መስተጋብር ምግብን ለመመገብ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው ? እንደ መመገብ ያሉ የመጀመሪያ ክህሎቶች የሚኖሩን ስንማራቸው ነው። የሚለመዱትም፣ ልጆች ከተንከባካቢዎቻቸው ጋር ባላቸው ግንኙነቶች እና ሁነቶች ነው፡፡ ለልጁ እድገት በተለይ ለምገባ ደንብ ወይም ተረጋግቶ የመቀመጥ ችሎታው ወሳኝ ነው፡፡ አንድ ልጅ በደንብ መመገብ እንዲችል መጀመሪያ ተረጋግቶ መቀመጥ መቻል አለበት፡፡ አንዴ ከተረጋጉ ልጆች ከሌሎች ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲመሠርቱ እራሳቸውን እንዲመገቡ እና እራሳቸውን ለመመገብ የበለጠ ጥሩ ዕድል አላቸው፡፡ ልጆች ተረጋግተው እንዲቀመጡ ከተንከባካቢዎቻቸው ተጨማሪ እገዛ ይፈልጋሉ፡፡ ከተንከባካቢዎች ጋር አስተማማኝ ደህንነቱ የተጠበቀ እና አወንታዊ ግንኙነቶች መኖር ለልጆች እንዴት መረጋጋት እንዳለባቸው የመማሪያ የመጀመሪያ መንገድ ነው፡፡ ለልጁ እድገት በተለይ ለምገባ እና እራሱን ለመመግብ፣ በደንብ ወይም ተረጋግቶ የመቀመጥ ችሎታው ወሳኝ ነው፡፡

Transcript of ክፍል 1.10: የመስተጋብር መሰረታዊ - Holt International...መስተጋብር...

Page 1: ክፍል 1.10: የመስተጋብር መሰረታዊ - Holt International...መስተጋብር ማለት ምን ማለት ነው? መስተጋብር ማለት በሌላ አገላለፅ

ምእራፍ 1 | ክፍል 1 .10: የመስተጋብር መሰረታዊ ሐሳቦች

101

ክፍል 1.10: የመስተጋብር መሰረታዊ ሐሳቦች

መስተጋብር ማለት ምን ማለት ነው? መስተጋብር ማለት በሌላ አገላለፅ “ግንኙነት” ማለት ነው፡፡ እነዚህን ቃላቶች በዚህ መመሪያ ላይ እያለዋወጥን እንጠቀምባቸዋለን፡፡ ልጆች ከተንከባካቢዎቻቸው ጋር በየዕለቱ የሚጋሯቸው ግዜዎች የምገባን ግዜ ጨምሮ መስተጋብር ይባላል፡፡ ልጆች ጤናማ እንዲሆኑ እና እንዲበለፅጉ አዎንታዊ ፣ የታሰበባቸው ግንኙነቶች አስፈላጊ ናቸው፡፡ ልጁ ከአሳዳጊዎቹ ጋር ወጥነት እና ትኩረት ያለው ግንኙነት ሲኖረው፣ እድገቱ ይበልጥ ጠንካራ ይሆናል፡፡

በእብዛኛው ከሌሎች ጋር የሚከሰቱ አስደሳች ግንኙቶች የልጁን እድገት ያጠናክራሉ፡፡

መስተጋብር ምግብን ለመመገብ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? እንደ መመገብ ያሉ የመጀመሪያ ክህሎቶች የሚኖሩን ስንማራቸው ነው። የሚለመዱትም፣ ልጆች ከተንከባካቢዎቻቸው ጋር ባላቸው ግንኙነቶች እና ሁነቶች ነው፡፡ ለልጁ እድገት በተለይ ለምገባ ደንብ ወይም ተረጋግቶ የመቀመጥ ችሎታው ወሳኝ ነው፡፡ አንድ ልጅ በደንብ መመገብ እንዲችል መጀመሪያ ተረጋግቶ መቀመጥ መቻል አለበት፡፡ አንዴ ከተረጋጉ ልጆች ከሌሎች ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲመሠርቱ ፣ እራሳቸውን እንዲመገቡ እና እራሳቸውን ለመመገብ የበለጠ ጥሩ ዕድል አላቸው፡፡ ልጆች ተረጋግተው እንዲቀመጡ ከተንከባካቢዎቻቸው ተጨማሪ እገዛ ይፈልጋሉ፡፡ ከተንከባካቢዎች ጋር አስተማማኝ ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና አወንታዊ ግንኙነቶች መኖር ለልጆች እንዴት መረጋጋት እንዳለባቸው የመማሪያ የመጀመሪያ መንገድ ነው፡፡

ለልጁ እድገት በተለይ ለምገባ እና እራሱን ለመመግብ፣ በደንብ ወይም ተረጋግቶ የመቀመጥ ችሎታው ወሳኝ ነው፡፡

Page 2: ክፍል 1.10: የመስተጋብር መሰረታዊ - Holt International...መስተጋብር ማለት ምን ማለት ነው? መስተጋብር ማለት በሌላ አገላለፅ

ምእራፍ 1 | ክፍል 1 .10: የመስተጋብር መሰረታዊ ሐሳቦች

102

የመስተጋብር ዋና ዋና ክፍሎች: የላቀ ተንከባካቢ ባሕርያት በዚህ ክፍል ውስጥ ውጤታማ እና እጅግ በጣም ጥሩ ተንከባካቢ የሚያደርጉ ቁልፍ ነገሮች እናብራራለን ፡፡ እጅግ በጣም ጥሩ ተንከባካቢነት ከባለአደራ ተንከባካቢ የተለየ ነው ፡፡ አንድ ሰው የሕፃናትን መሠረታዊ ፍላጎቶች የሚንከባበብ (ለምሳሌ ፣ ምግብ ፣ ውሃ እና እንደ መታጠቢያ ፣ ዳይፐር እና ሽንት ቤት ያሉ ሌሎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች የሚረዳ) ከሆነ ባለአደራ ተንከባካቢ ይባላል፡፡ እጅግ በጣም ጥሩ ተንከባካቢ ማለት አንድ ሰው የልጆችን የዕለት ተዕለት ፍላጎቶች ሲንከባከብ ብቻ ሳይሆን አዎንታዊ እና አፍቃሪ ግንኙነቶችም ሲሰጡ ነው ፡፡ እነዚህ አወንታዊ እና ትርጉም ያላቸው ግንኙነቶች ወደ ጤናማ ውጤቶች እንዲያመራ በማድረግ የሕፃናትን ሕይወት ጥራት ያሻሽላሉ ፡፡ ተንከባካቢዎች ሁሉንም ልጆች በሚደግፉበት ጊዜ እነዚህን አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ከግምት ውስጥ ማስገባት በጣም አስፈላጊ እና ጥሩ እንክብካቤን እንዴት መስጠት እንደሚችሉ እንዲማሩ ማድረጉ አስፈላጊ ነው::

ምቹ መሆን ማለት የሕፃናትን ፍላጎቶች በከፍተኛ ሁኔታ ማወቅ ማለት ነው

ከቀልቡ የሆነ ፣ ትኩረት የሰጠ፣ ግልፅ እና ምቾት የተሞላበት እንክብካቤ

የብቁ ተንከባካቢ ምርጥ ባህሪዎች

ከቀልቡ የሆነ ከልጁ ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ወቅት በአካል እና በአዕምሮ ውስጥ ሙሉ በሙሉ መገኘት ፡፡ ከልጁ ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ወቅት በአካል እና በአዕምሮ ሙሉ በሙሉ መገኘት ፡፡ ተንከባካቢዎች በወቅቱ የሚከሰቱ ነገሮችን በትኩረት ይከታተላሉ (ማለትም ፣ መሰራት ስላለበት ስራ ማሰብ አይደለም) አንድ ልጅ ምን እንደሚፈልግ መረዳት እና እነዚያን ፍላጎቶች እንዴት በተሻለ መንገድ እንደሚሟላለት መረዳት ነው። “እኔ አያለሁ እና ታየኛለህ”፡፡

ትኩረት

የሰጠ

የልጆችን አካላዊ እና ስሜታዊ ፍላጎቶች በትኩረት ይከታተሉ። ተንከባካቢዎች የሕፃን ልጅ ፍላጎቱን እንደተረዱት እንዲሰማዉ በትኩረት ያዳምጣሉ። ልጆች ተንከባካቢዎቻቸው በትኩረት እንደሚሰሟቸው እና እንደሚመከቷቸው መሆናቸውን ሲያውቁ ፍላጎቶቻቸውን እና ስሜታቸውን መግለፃቸውን ይቀጥላሉ ፡፡ “ተረድተኸኛል ፣ ያ ደግሞ ጥሩ ስሜት እንዲሰማኝ ያደርገኛል ፡፡ ”

ግልፅ

ለልጁ ፍላጎቶች መልስ ለመስጠት ወጥ እና ፈጣን ይሁኑ። ተንከባካቢዎች በሰዓቱ ምላሽ ይሰጣሉ እና ልጆች ተንከባካቢዎች ደህንነታቸውን እንደሚጠብቁ ማመንን ይማራሉ። ወጥ በሆነ መልኩ የሚደረግ እንክብካቤ (ለምሳሌ ፣ አንድ አይነት ተንከባካቢ ፣ የጊዜ ሰሌዳ ፣ ጡጦ / ኩባያ / ማንኪያ ፣ የመመገቢያ ክፍል ፣ የመመገቢያ ቦታ ፣ ወዘተ) ምላሽ በሚሰጥበት ጊዜ ልጆች ለህይወት አስፈላጊ የሆኑ ጠንካራ ግንኙነቶችን ያዳብራሉ ፡፡ “ከአንቺ ጋር ደህንነት ይሰማኛል ፡፡ ሁሌም ለእኔ እዚህ ነሽ።.”

ምቾት

የተሞላበት

ከልጅ ጋር በጥልቀት ይገናኙ እና የእሷን የግል ፍላጎቶችዋን እና ምኞቶችዋን ይረዱ፡፡ ተንከባካቢዎች ለእያንዳንዱ ልጅ በተከታታይ እና በአክብሮት ምላሽ ለመስጠት የልጁን ፍላጎቶች በግልፅነት (ለሚመጣ ለውጥ ዝግጁ ሆነው) ፍላጎቶች ይመለከታሉ። ይህ ለአንድ ልጅ የአመኔታን ስሜት ይፈጥራል ፡፡ ““ሁልጊዜ ጥሩ ስለምትንከባከቡኝ እተማመናለሁ።”

Page 3: ክፍል 1.10: የመስተጋብር መሰረታዊ - Holt International...መስተጋብር ማለት ምን ማለት ነው? መስተጋብር ማለት በሌላ አገላለፅ

ምእራፍ 1 | ክፍል 1 .10: የመስተጋብር መሰረታዊ ሐሳቦች

103

ከእያንዳንዱ ልጅ ጋር ስለሚኖር መስተጋብር የሚጠቅሙ ምክሮች

ጠቃሚ ምክር 1:

ጤናማ ግንኙነቶች የአእምሮን እድገት ያግዛሉ ፡፡ በልጆች እና በተንከባካቢዎች መካከል ያሉ መልካም ግንኙነቶች የሕፃናትን አእምሮ እድገት እና መዳበርን ይደግፋሉ ፡፡ ጠንካራ አእምሮ ከተንከባካቢዎች ጋር ከነበረ የጥሩ ጊዜያት ውጤት ነው ፡፡

ጠቃሚ ምክር 2:

ጤናማ ግንኙነቶች አእምሮን ለመፈወስ ይረዳሉ ፡፡ ሕፃናት ያጋጠሟቸውን የውጥረቶች እና የችግሮች ተፅእኖ ለመቀነስ ከተንከባካቢዎቻቸው ጋር ያላቸው አዎንታዊ ግንኙነቶች ቀዳሚ መንገዶቾ ናቸው፡፡ ከቀልብ በመሆን ፣ ትኩረት በመስጠት ፣ ምላሽ ሰጭ እና ምቹ በመሆን ተንከባካቢዎች አዎንታዊ ግንኙነቶችን መፍጠር ይችላሉ።

ጠቃሚ ምክር 3:

ጤናማ ግንኙነቶች ልጆች እንዲያብቡ ይረዳቸዋል ፡፡. በተንከባካቢዎቻቸው በአዎንታዊ መስተጋብሮች ያደጉ ልጆች በእውነቱ ጤናማ እና የበለጠ የተስተካከለ (አካልና አእምሮ) ናቸው ፡፡

ጠቃሚ ምክር 4:

እጅግ በጣም ጥሩ ተንከባካቢ ተጨማሪ ጊዜ አይወስድም። ተንከባካቢዎች በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች እና ተግባራቶች ላይ ቀላል የሆኑ ስልቶች በመጠቀም አዎንታዊ ግንኙነቶችን ይተገብራሉ፡፡

ጠቃሚ ምክር 5:

ልጆች ከአዎንታዊ ግንኙነቶች አውድ በተሻለ ይማራሉ። በምግብ ሰዓት (እና ከዚያ በኋላ) ከልጅ ጋር አወንታዊ ግንኙነቶችን መፍጠር የትምህርት ሂደትን ለመደገፍ በጣም ጥሩው መንገድ ነው፡፡

የመደምደሚያ ሃሳቦች

ጤናማ ግንኙነቶች ጤናማ ልጆችን ለማሳደግ መሠረት ናቸው ፡፡ ልጆች ከመጀመሪያው ጀምሮ ጥሩ ተንከባካቢዎች ሲያገኙ ለቀሪው ህይወታቸው ጉልህ ጥቅሞችን ያገኛሉ ፡፡ ልጆች በቋሚነት የሚተማመኑበት ሰው

ከሌላቸው ፣ እና አወንታዊ ግንኙነቶች ካልነበሯቸው ፣ እድገታቸው እና ጉልብትናቸው በከፍተኛ ደረጃ የተገታ ይሆናል፡፡ ይህ ትናንሽ እና አነስተኛ ኃይል ያላቸው አንጎልዎችን እና አካላትን እንዲኖራቸው ፣ ከሌሎች ጋር እንዴት መገናኘት እና መዛመድ እንደሚቻል መማርን እንዲሁም በማህበረሰባችን ውስጥ ስኬታማ ጎልማሶች መሆንን ያካትታል ፡፡ በዚህ ምክንያት ተንከባካቢዎች አካላዊ ጥንካሬ ያላቸውን ልጆች ብቻ ሳይሆን ስሜታዊ ጠንካራ ልጆችን ለማሳደግ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ ፡፡ በቀኑ ውስጥ እያንዳንዱ እንቅስቃሴ እና የሚዘወተሩ ድጊቶች በልጁ ሕይወት ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖ ለማሳደር እድል ናቸው ፡፡

በእያንዳንዱ እንቅስቃሴ እና የሚዘወተሩ ድርጊቶች ጊዜ መስተጋብርን የሚደግፉበት ልዩ መንገዶች እና ተጨማሪ መንገዶች ከፈለጉ ፣ ምእራፍ 8 እና አባሪ 9K ይመልከቱ ፡፡

Page 4: ክፍል 1.10: የመስተጋብር መሰረታዊ - Holt International...መስተጋብር ማለት ምን ማለት ነው? መስተጋብር ማለት በሌላ አገላለፅ